ብቁነት
ለማመልከት ከዚህ በታች ያሉትን ሁሉንም መስፈርቶች ማሟላት አለብዎት፦
የኪንግ ካውንቲ የእርዳታ ፈንድ በኢሚግሬሽን ሁኔታቸው ምክንያት ለሥራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች ወይም ለፌደራል ማነቃቂያ ገንዘብ ብቁ ያልሆኑትን የኪንግ ካውንቲ ስደተኛ ነዋሪዎችን የሚደግፍ የ $8,000,000 የገንዘብ ድጋፍ ነው።
ማመልከቻው ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 6 ቀን 2022 የሚከፈት ሲሆን የእርዳታ ገንዘብ እስኪያልቅ ድረስ ክፍት ይሆናል።
ማመልከቻዎች በየሳምንቱ የሚገመገሙ ሲሆኑ አዳዲስ ውሳኔዎች ከሴፕቴምበር 20 በኋላ ይላካሉ።
ማመልከቻው ገንዘቡ ካለቀ በኋላ ይዘጋል።
ማመልከቻዎን በማስገባት ላይ አጋሮቻችን ከአንዱ እገዛን ማግኘት ይችላሉ። በመረጡት ቋንቋ እገዛ ለማግኘት፣ እባክዎን ከታች የተዘረዘረውን የማህበረሰብ አጋር ያግኙ።
ስለ ኪንግ ካውንቲ የእርዳታ ፈንድ ጥያቄዎች አሉዎት?
የኪንግ ካውንቲ የእርዳታ ፈንድ በኢሚግሬሽን ሁኔታቸው ምክንያት ለሥራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች ወይም ለፌደራል ማነቃቂያ ገንዘብ ብቁ ያልሆኑትን የኪንግ ካውንቲ ስደተኛ ነዋሪዎችን የሚደግፍ የ $8,000,000 ፕሮግራም ነው።
አዎ። ይህ የገንዘብ ድጋፍ በኢሚግሬሽን ሁኔታቸው ምክንያት ለፌደራል ጥቅማጥቅሞች ብቁ ላልሆኑ ግለሰቦች የታሰበ ነው።
አብዛኛውን ጊዜ፣ አይደሉም። ስደተኞች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና የ DACA ተቀባዮች፣ የሥራ ፈቃድ አላቸው እናም የሥራ አጥነት ጥቅማጥቅሞችን ሊያገኙ ይችላሉ። እንዲሁም ብዙዎቹ ከፌዴራል ማነቃቂያ ክፍያዎችም የገንዘብ ድጋፍ አግኝተዋል።
አይ. እያንዳንዱ ብቁ ሰው የእራሱን የግል ማመልከቻ መሙላት አለበት። አመልካቾች ለማመልከት ቢያንስ ዕድሜያቸው 16 ዓመት መሆን አለበት።
No. Each eligible person must complete their own individual application. Applicants must be at least 16 years of age to apply.
አይ። እያንዳንዱ ብቁ ሰው የእራሱን የግል ማመልከቻ መሙላት አለበት። አመልካቾች ለማመልከት ቢያንስ ዕድሜያቸው 16 ዓመት መሆን አለበት።
ብቁ ከሆኑ እና የወረቀት ቼክ ወይም የስጦታ ካርድ ለመቀበል ከመረጡ፣ ክፍያዎን በዋሽንግተን ስቴት ውስጥ ወደሚያምኑት ሰው አድራሻ መላክ ይችላሉ።
ከዝርዝር ሀ ለማንነትዎ እና ቤት አልባ ከመሆንዎ በፊት በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ይኖሩ፣ ይሠሩ ወይም ይማሩ እንደነበር ማረጋገጫ የሚያቀርብ ወቅታዊ ሰነድ ካለዎት፣ በማመልከቻው ላይ ማቅረብ ይችላሉ።
ከዝርዝር ሀ ሰነድ ከሌልዎት፣ ማንነትዎን የሚያረጋግጥ ሰነድ ከዝርዝር ለ እንዲሁም በኪንግ ካውንቲ ውስጥ እንደሚኖሩ፣ እንደሚሠሩ ወይም እንደሚማሩ በማረጋገጥ፣ በዝርዝር ሐ ከተዘረዘሩት ሰዎች በአንዱ የተፈረመ እና ቀን የተጻፈበት ደብዳቤ ማቅረብ ይችላሉ።
ከዝርዝር ሀ ማንነትዎን እና በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ነዋሪ መሆንዎን የሚያረጋግጥ ወቅታዊ ሰነድ ካለዎት፣ እባክዎን ቤት አልባ ከመሆንዎ በፊት የነበረውን የኪንግ ካውንቲ አድራሻ ያስገቡ።
የአሁኑ የዝርዝር ሀ ሰነድ ከሌለዎት እና የዝርዝር ለ (ማንነት) እና የዝርዝር ሐ (የነዋሪነት) ሰነድ እያቀረቡ ከሆነ፣ እባክዎን በዝርዝር ሐ ሰነድዎ ውስጥ የተዘረዘረውን አድራሻ ያስገቡ።
አዎ። ከኪንግ ካውንቲ ውጭ የሚኖሩ ከሆነ ማመልከት ይችላሉ፣ ነገር ግን በኪንግ ካውንቲ ወሰን ውስጥ የሚሠሩ ከሆነ ወይም በኪንግ ካውንቲ ወሰን ውስጥ ከተማሩ ወይም በኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ከታሰሩ ነገር ግን ከመታሰሩ በፊት በኪንግ ካውንቲ ውስጥ የኖሩ፣ የሠሩ ወይም የተማሩ ከሆነ ብቻ ነው።
በተጨማሪም፣ ኪንግ ካውንቲ ለኢሚግሬሽን ሂደት ለሚያመለክቱ ወይም ውስጥ ለሆኑ ስደተኛ ነዋሪዎች የገንዘብ እርዳታ የሚሰጠውን የኪንግ ካውንቲ የኢሚግሬሽን ክፍያ ድጋፍ ፕሮግራም እያቀረበ ነው። እዚህ ማመልከት ይችላሉ: kcfeesupport.org/
በተጨማሪም፣ የዋሽንግተን የኮቪድ-19 የስደተኞች እርዳታ ፈንድ (Washington COVID-19 Immigrant Relief Fund) በኢሚግሬሽን ሁኔታቸው ምክንያት ለፌዴራል ማነቃቂያ ገንዘብ ወይም ለሥራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች ብቁ ላልሆኑ ስደተኛ ነዋሪዎች የሚሰጥ የስቴት አቀፍ ፈንድ ነው። ይህ ማመልከቻ ሴፕቴምበር ውስጥ ይከፈታል። ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት እዚህ መመዝገብ ይችላሉ፡ https://actionnetwork.org/forms/sign-up-for-updates-from-waisn
በገንዘብ ውስንነት ምክንያት ሁሉንም ሰው ማገልገል አልቻልንም። አንዳንድ ብቁ አመልካቾች የገንዘብ ድጋፍ ላያገኙ ይችላሉ።
በገንዘብ ውስንነት ምክንያት ሁሉንም ሰው ማገልገል አልቻልንም። በጣም የሚያስፈልጋቸውን ለመደገፍ ሲባል፣ በፍላጎት ላይ በመመስረት ለአመልካቾች ቅድሚያ እየሰጠን ነው።
የኪንግ ካውንቲ የእርዳታ ፈንድ ሴፕቴምበር 6 ይከፈታል።
ምንም የማመልከቻ ማብቂያ ቀን የለም። ገንዘቡ እስኪያልቅ ድረስ ማመልከቻው ክፍት እንደሆነ ይቆያል።
ማንነትዎን እና የኪንግ ካውንቲ ነዋሪነትዎን የሚያረጋግጡ ሊነበቡ የሚችሉ ሰነዶች ያስፈልጉዎታል። ከዚህ በታች ያለው ሰንጠረዥ ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው ሰነዶች ምሳሌዎችን ይሰጣል። እባክዎን ከዝርዝር ሀ የአንድ ንጥል ወይም ከሁለቱም ከዝርዝር ለ እና ዝርዝር ሐ የአንድ ንጥል በግልጽ የሚታይ ቅጂ እንዳለዎት ያረጋግጡ።
Click to view the Required Documents
አዎ። እያንዳንዱ ብቁ ሰው የእራሱን የግል ማመልከቻ መሙላት አለበት።
ነገር ግን፣ በቤተሰብዎ ውስጥ ስላሉት የጎልማሶች እና የልጆች ብዛት መረጃ እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ። ይህ መረጃ የቤተሰብዎን ገቢ ለመወሰን ብቻ ጥቅም ላይ ይውላል። የእርስዎ ቤተሰብ ከእርስዎ ጋር ሂሳቦችን (ምግብ፣ ወጪ፣ ወዘተ) የሚጋሩትን ወይም ለገንዘብ ድጋፍ በእርስዎ ላይ ጥገኛ የሆኑትን ወይም በገንዘብ የምደግፉትን ሰዎች ያካትታል።
ማመልከቻዎች የሚገቡት በግል ነው። እያንዳንዱ ብቁ ሰው የእራሱን ማመልከቻ ማስገባት አለበት። አመልካቾች ለማመልከት ቢያንስ ዕድሜያቸው 16 ዓመት መሆን አለበት።
ነገር ግን፣ በቤተሰብዎ ውስጥ ስላሉት የጎልማሶች እና የልጆች ብዛት መረጃ እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ። ይህ መረጃ የቤተሰብዎን ገቢ ለመወሰን ብቻ ጥቅም ላይ ይውላል። የእርስዎ ቤተሰብ ከእርስዎ ጋር ሂሳቦችን (ምግብ፣ ወጪ፣ ወዘተ) የሚጋሩትን ወይም ለገንዘብ ድጋፍ በእርስዎ ላይ ጥገኛ የሆኑትን ወይም በገንዘብ የምደግፉትን ሰዎች ያካትታል።
ለገንዘብ ድጋፉ ብቁ የሆነ እያንዳንዱ ሰው ማመልከት የሚችል ሲሆን የእራሳቸውን የግል ማመልከቻ መሙላት አለባቸው።
ማመልከቻውን ማቅረብ የምንችለው ከኢንተርኔት ጋር በተገናኘ ኮምፒውተር ወይም ተንቀሳቃሽ መሳሪያ መሙላት በሚችሉበት በዚህ የኦንላይን ፖርታል በኩል ነው። የማመልከቻ እርዳታ ለማግኘት፣ ከኢንተርኔት ጋር የተገናኘ መሳሪያ ማግኘት ካልቻሉ፣ እባክዎን የዋሽንግተን ስድተኛ አንድነት ኔትወርክን (Washington Immigrant Solidarity Network) በ 1 (844) 724-3737 ወይም ከታች ካሉት ሌሎች አጋር ድርጅቶቻችን አንዱን ያግኙ፦
እባክዎን ለሁሉም አመልካቾች የማስረከቢያ መታወቂያቸውን ይስጡ እና ያንን እንዲጽፉ እና/ወይም ፎቶ እንዲያነሱ እና የሆነ ቦታ እንዲያስቀምጡ ይንገሯቸው። ይህ ቁጥር የማመልከቻቸውን ሁኔታ ለመከታተል በጣም አስፈላጊ ነው።
ማመልከቻዎ ከገባ በኋላ መረጃ ማሻሻስ ወይም ስህተትን ማስተካከል ከፈለጉ፣ እባክዎን የተሻሻለ መረጃዎን የያዘ አዲስ ማመልከቻ ያስገቡ።
በሚጠበቀው ከፍተኛ የማመልከቻ ብዛት ምክንያት፣ የይግባኝ ሂደት አይኖርም።
የእርስዎ ቤተሰብ በስህተት ብዙ ማመልከቻዎችን ካስገባ፣ Scholar Fund (Scholarship Junkies) ከአንድ ቤተሰብ የመጡ ብዙ ማመልከቻዎች እንደገቡ ማወቅ የሚችል ሲሆን ከፍተኛ ፍላጎት የሚያሳየውን ማመልከቻ ይገመግማል። እንዲሁም የማመልከቻ ችግሮችን ካወቁ፣ አመልካቾችን በስልክ ወይም በጽሑፍ ማግኘት ይችላሉ።
ማመልከቻዎችን በየሳምንቱ እንገመግማለን። ማመልከቻዎ ከተገመገመ በኋላ፣ ማሳወቂያዎች ከመለያዎ ጋር በተገናኘው የኢሜል አድራሻ እና በጽሁፍ መልዕክት በኩል ይላካሉ። የማመልከቻዎን ሁኔታ በማንኛውም ጊዜ https://www.kingcountyrelief.org/status ላይ መመልከት ይችላሉ። ማመልከቻዎችን በምንገመግምበት እና ከፍተኛ ፍላጎት ላላቸው ሰዎች ቅድሚያ በምንሰጥበት ጊዜ፣ እባክዎን በትዕግስት ይጠብቁ።
በአንድ ብቁ ሰው $1,000 የአንድ ጊዜ የቀጥታ ክፍያ ለመቀበል ማመልከት ይችላሉ። ገንዘቡን በቼክ፣ በስጦታ ካርድ (ቪዛ) ወይም በቀጥታ የባንክ ሂሳብዎ ተቀማጭ (ACH) በሚደረግ መልክ መቀበል ይችላሉ።
ብቁ የሆኑ አመልካቾች የአንድ ጊዜ ክፍያ ብቻ ነው መቀበል የሚችሉት።
ክፍያዎች ከሴፕቴምበር 20 በኋላ ጀምሮ በሳምንቱ ለህብረተሰቡ ይለቀቃሉ። በፖስታ የተላኩ ቼኮች እና የስጦታ ካርዶች ለመቀበል ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስዱ ይችላሉ እናም የሽልማት ማስታወቂያ ከተሰጠዎት በኋላ ሁሉም ሰው በ 14 ቀናት ውስጥ ክፍያ ይቀበላል ብለን እንጠብቃለን።
ክፍያዎችን ለመቀበል ሦስት አማራጮች አሉ፦ ምልክት ያድርጉ፦ በአካል የሚሰጥ የማስተርካርድ ስጦታ ካርድ፦ በቀጥታ ተቀማጭ ገንዘብ
አዎ። የመኖሪያ አድራሻ በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ነዋሪ መሆንን ለማሳየት ይጠቅማል። የፖስታ መላላኪያ አድራሻ፣ አድራሻው በዋሽንግተን ስቴት ውስጥ እስካለ ድረስ የፖስታ ሳጥን ቁጥር ወይም የእነሱን መልዕክት የሚቀበሉበት እና/ወይም ለመቀበል የበለጠ ምቾት የሚሰማዎት ማንኛውም አድራሻ ሊሆን ይችላል።
አዎ፣ ተቀባይነት ካገኙ በኋላ የመክፈያ ዘዴዎን መቀየር ይችላሉ። እባክዎን ስምዎን፣ የማስረከቢያ መታወቂያዎን እና ምን አይነት የክፍያ መንገድ እንደምመርጡ በመስጠት፣ Scholar Fund ን በ 206-203-6536 ወይም በ Payments@kingcountyrelief.org ላይ ያግኙ።
የስጦታ ካርድዎን ተጠቅመው ከኤቲኤም ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ ነገር ግን በኤቲኤም ላይ በመመስረት የማስወጫ ክፍያ ወይም ገደብ ሊጣልብዎት ይችላል።
አይ። በዩኤስ የዜግነት እና ኢሚግሬሽን አገልግሎት (USCIS) መሰረት እንደዚህ ፕሮግራም ያሉ “የአደጋ ጊዜ እርዳታ” ጥቅማጥቅሞች አንድ ግለሰብ የመንግስት ጥገኛ (public charge) መሆን አለመሆኑን ለመወሰን አይታይም። ለበለጠ መረጃ ይህንን የ USCIS የመንግስት ጥገኛ (public charge) መረጃ ወረቀት ማንበብ ይችላሉ። ስለ እርስዎ የኢሚግሬሽን ሁኔታዎ እና/ወይም የጥቅማጥቅሞች ጥያቄዎች ካሉዎት፣ ከኢሚግሬሽን ጠበቃ ወይም በ DOJ እውቅና ካለው ተወካይ ጋር መነጋገር አለብዎት ።
ከኪንግ ካውንቲ የስደተኞች እርዳታ ፈንድ መቀበል የዩኤስ ዜጋ የመሆን ችሎታ ላይ ተጽዕኖ አይኖረውም። እንዲሁም ህጋዊ ቋሚ ነዋሪ/ግሪን ካርድ ባለቤት የሆነ የቤተሰብ አባል የአሜሪካ ዜጋ የመሆን ችሎታ ላይ ተጽዕኖ አይኖረውም። ስለ እርስዎ የኢሚግሬሽን ሁኔታ እና/ወይም የጥቅማጥቅሞች ጥያቄዎች ካሉዎት፣ ከኢሚግሬሽን ጠበቃ ወይም በ DOJ እውቅና ካለው ተወካይ ጋር መነጋገር አለብዎት።
አይ፣ ሁሉም ክፍያዎች በእርዳታ የሚደረጉ እና በ IRS መሰረት የአደጋ ጊዜ እርዳታ ተብሎ የተመደቡ ሲሆኑ ግብር እንደሚከፈልበት ገቢ መካተት የለባቸውም።
ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት Scholar Fund (Scholarship Junkies) የእርስዎን መረጃ በፈቃደኝነት ኪንግ ካውንቲን ጨምሮ ከመንግስት አካላት ጋር አያጋራም። የ Scholar Fund ለኪንግ ካውንቲ የእርዳታ ፈንድ (King County Relief Fund) በኦንላይን ማመልከቻ ላይ በፈቃደኝነት የሚያቀርቡትን የግል መረጃ የመሰብሰብ ኃላፊነት አለበት። ያልተፈቀደ መዳረሻን ለመከላከል፣ የመረጃ ትክክለኛነትን ለመጠበቅ እና የመረጃን ትክክለኛ አጠቃቀም ለማረጋገጥ እንዲያግዝ፣ Scholar Fund (Scholarship Junkies) የሚሰበሰቡትን መረጃዎች ለመከላከል እና ለመጠበቅ ተገቢ አካላዊ፣ ኤሌክትሮኒካዊ እና የአስተዳደር ሂደቶችን አዘጋጅቷል። ስለ Scholarship Junkies አጠቃላይ የግላዊነት ፖሊሲ (በእንግሊዝኛ ብቻ) የበለጠ እዚህ ማወቅ ይችላሉ።
የግል መረጃ በፍቃደኝነት ለመንግስት፣ የዩኤስ ኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ አስፈጻሚ ወይም ለ ICE፣ ለሌላ ህግ አስከባሪ አካል፣ ለአከራይዎ፣ ለአሠሪዎ ወይም ለሌላ ሰው በጭራሽ አይጋራም። ሁሉም መረጃ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በሚስጥራዊ ቅርጸት ስለሚከማች ሊደረስበት አይችልም።
ከኪንግ ካውንቲ ጋር ባለን ውል መሰረት የአመልካቹን ግላዊ መረጃ ማግኘት የሚችሉት ብቸኛ ሰዎች Scholar Fund (Scholarship Junkies፣ ፈንዱን የሚያስተዳድር የማህበረሰብ ድርጅት) ናቸው። የእርስዎን መረጃ ለሌላ ለማንም አናጋራም። ነገር ግን ህጋዊ የመጠየቂያ ወረቀት ካለ፣ በህጋዊ መንገድ የግል መረጃን እንድንለቅ ልንገደድ እንችላለን። ይህ የመሆን ዕድሉ አነስተኛ ነው፣ ግን የማይቻል አይደለም።
በኪንግ ካውንቲ የኢሚግሬሽን ክፍያ ድጋፍ ፕሮግራም ማንን እያገለገልን እንዳለን በተሻለ ለመረዳት የስነ ህዝብ ጥያቄዎች ይጠየቃሉ። የእርስዎ ምላሾች በብቁነትዎ ላይ ምንም ተጽዕኖ አይኖራቸውም፣ እንዲሁም ማንኛውንም የስነ ሕዝብ መረጃ ላለማሳወቅ መምረጥ ይችላሉ። ያቀረቡት መረጃ ከስምዎ ጋር ተያይዞ ለኪንግ ካውንቲ ወይም ለሌላ የመንግስት ኤጀንሲ በጭራሽ አይጋራም።
ማጭበርበርን ለመለየት፣ ድግግሞሽን ለማስወገድ እና የቤተሰብ ክፍያ ገደቦችን ለማስጠበቅ፣ Scholar Fund (Scholarship Junkies) ልዩነቶችን ለመለየት አመልካቾችን ለማጣራት እና ለማረጋገጥ በርካታ ስልቶችን አዘጋጅቷል፣ ይህም የተሟላ የማመልከቻ ግምገማ ሂደትን፣ የማጭበርበሪያ መልዕክት ማጣሪያዎችን እና የአድራሻ ማረጋገጫዎችን ያካትታል። እንዲሁም የማመልከቻ ችግሮችን ካወቁ፣ አመልካቾችን በስልክ ወይም በጽሑፍ ማግኘት ይችላሉ።
አንድ አመልካች ብዙ ጊዜ ተቀባይነት እንዳገኘ እና/ወይም የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገለት ካወቁ፣ እባክዎን ለ Scholar Fund በ 206-203-6536 ወይም support@kingcountyrelief.org ያሳውቁ። አመልካቾች የተለያዩ ስሞችን ወይም ትንሽ ለየት ያለ መረጃን በመጠቀም የሚያመለክቱ ከሆነ፣ ድግግሞሽ ማስቀረትን አስቸጋሪ ያደርገዋል። ነገር ግን፣ ክፍያው ወጪ ካልተደረገ ክፍያ ማቆም እንችላለን።
የገቢ ብቁነት ገበታ